fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የጧት ፀሐይ የማስታወስ ችሎታን ሊያዳብር ይችላል – ተመራማሪዎች

ብዙ ጊዜ የማስታወስ ችግርያጋጥሞታል? እንደግዲያው በቻይና የሚገኙ ተመራማሪዎች ለዚህ ምናልባትም መድሐኒት ሊሆን የሚችል ነገር አግኝተናል ይላሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ ከቤት ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ፀሐያ መሞቅ የማስታወስ ችሎታችንን ሊያዳብሩት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በቻይና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኙ ተመራማሪዎች ጉዳት የማያስከትል የጨረር ወይንም አልትራ ቫዮሌት አዕምሮዋችን ውስጥ ያለውን ህዋስ ያነቃቃል ብለዋል፡፡

ሆኖም ይህ አልትራ ቫዮሌት በተባለው ጨረር ከበቂ በላይ የሚጋለጡ ከሆነ ከቆዳ ጋር በተያያዙ በሽታዎች የመያዝ እድልንም ከፍ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ጥናቱን የመሩት ቻይናዊ የጧት ፀሐይ የቪታሚን ዲ ስራ በማቀላጠፍ ለበርካታ የቆዳ በሽታዎች ፍቱን መድሐኒት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በምርምር መጽሔቱ ላይ አዕምሮ በምን መልኩ ስራውን እንደሚያካሂድ ለማወቅ ትልቅ እምርታ ነው ብለዋል የጥናቱ መሪ፡፡

 

 

 

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram