fbpx
AMHARIC

የጦር መሳሪያ ምስል ግንባሩ ላይ በመነቀስ በህግ የተቀጣው ግለሰብ

የጦር መሳሪያ መከልከሉ ከታወቀ የጦር መሳሪያን በሰውነታቸው ላይ የሚነቀሱ ህገ ወጥ ናቸው ብለው ያስባሉ?

የጦር መሳሪያን የፊት ገጽታ ላይ መነቀስ የሚሰጠው ተጨማሪ ውበትስ ሊኖር ይችላልን ?

በአሜሪካ ደቡብ ካርሎኒያ ግዛት የጦር መሳሪያ ምስል ግንባሩ ላይ የተነቀሰ ወጣት በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ጥፋተኛ መባሉ ተገልጿል።

የደቡብ ካርሎኒያው ሚቼል ቪንስ ቀደም ሲል በተመዘገበበት የወንጀል ሪከርድ የጦር መሳሪያ እንዳይዝ የተከለከለና የጦር መሳሪያ በግንባሩ ላይ ተነቅሶ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

የ24 ዓመቱ ሚቼል ቪንስ ባሳለፍነው ቅዳሜ መኪና ውስጥ የተከለከለ ጦር መሳሪያ ይዞ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ማየታቸውንና መሳሪያውንም ለመደበቅ ሙከራ ሲያደርግ የወንጀል ሪከርዱ የተመዘገበበት መሆኑ ታውቋል።

ከዚህም ሌላ ከፍጥነት በላይ በማሽከርከርና ሌሎች የትራፊክ ህጎችን በመተላለፉ የጥፋተኞች መዝገብ ላይ ስሙ የሰፈረ መሆኑን ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ቀደም ሲል የቪነስን የጦር መሳሪያ በእዝግቢትነት የያዘው የግሪን ቪሌ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ሳያስፈልገው ወጣቱን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ጥፋተኛ መባሉን ሁፊንግቶንፖስት ዶት ኮም በዘገባው አስነብቧል።

ምንጭ፦ huffingtonpost.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram