የጥገኝነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ኢትዮጵያዊ ወጣት የራሱን ህይወት

(አድማስ ሬዲዮ) የጥገኝነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ኢትዮጵያዊ ወጣት የራሱን ህይወት አጠፋ

ነገሩ አሳዛኝ ነው፣ ወጣቱ ኢዮብ ተፈራ ይባላል፣ ባህር አቋርጦ፣ በረሃ ሰንጥቆ፣ ከአጋቾች ተርፎ ከሊቢያ ተነስቶ እንግሊዝ አገር ለመድረስ በርካታ ጊዜ ፈጅቶበታል። በዚህ ሳምንት ከወደ እንግሊዝ እንደተሰማው፣ ኢዮብ ተፈራ በሚኖርበት አካባቢ በሚገኝ ውሃ ውስጥ ሰምጦ የራሱን ህይወት አጥፍቷል። ምክንያቱ ደግሞ በተደጋጋሚ ያቀረበው የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት ሊያገኝ ባለመቻሉ ነው።

ዜናው እንደሚለው ኢዮብ እንግሊዝ የደረሰው ባለፈው 2005 ዓ.ም ነበር፣ ወዲያው ያቀረበው የጥገኝነት ጥያቄ ውድቅ ይደረግበታል። ከዚያም ቆይቶ እንደገና ቢሞክርም አልተሳካለትም። በብዙ እንግልት እንግሊዝ የደረሰው ኢዮብ ተፈራ፣ የቅርብ ጓደኛው በመንገድ ላይ ሞቶበታል። አይ ሲ ስ በሊቢያ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ባይኑ አይቷል። ይህ ሁሉ አ ዕምሮው ላይ ጫና እንደፈጠረበት ነው የ እንግሊዝ ፖሊስ የሚናገረው።

እናም ዕድሉ እንዳልተሳካለት ሲረዳ፣ ውሃ ውስጥ ሰምጦ የራሱን ህይወት እንዳጠፋ ነው የተነገረው።

የኢዮብ ተፈራ የቅርብ ጓደኛ መሃመድ ሰይድ ሲናገር “ኢዮብ ተምሮ ራሱን መለወጥና ቤተስቦቹን መርዳት ህልሙ ነበር፣ ግን የጥገኝነት ጥያቄው ውድቅ ሲደረግ ይህ ህልሙ የተናደበት አድርጎ ነው የተሰማው” ሲል በወቅቱ የተነበረውን ስሜት ተናግሯል።

ነፍስ ይማር!

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram