fbpx

የጋና እግር ኳስ ማህበር ከሙስና ጋር ተያይዞ በመንግስት እንዲበተን ተደረገ

የጋና እግር ኳስ ማህበር ከሙስና ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ መንግስት ትዕዛዝ እንዲበተን መደረጉ ተገለፀ።

የእግር ኳስ ማህበሩ ፕሬዚዳንት ኪዌሲ ንያንታከይ በእግር ኳስ ኢንቨስትመንት መሰማራት ከሚፈልግ ከአንድ የንግድ ሰው 65 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲቀበሉ የሚያሳይ ምስል ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው እንዲበተን የተደረገው ።

ይህ ክስ የቀረበባቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳነቱ በጉዳዩ ዙሪያ ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠታቸው ተነግሯል።
የሀገሪቱ ስፖርት ሚኒስትር ኢዚቅ አሳይማ የእግር ኳስ ማህበሩ በቀጥታ እንዲበተን ማደረጋቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የጋና የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሙስጠፋ አብደል ሀሚድ በበኩላቸው መንግስት እየተስፋፋ የመጣውን ህገ ወጥነት ተከትሎ የእግር ኳስ ፈዴሬሽኑ እንዲፈርስ መወሰኑን ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ የእግር ኳስ ማህበሩንን የሚመራ እስከሚዋቀር በጊዜያዊነት የሚመሩት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

የእግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ኪዌሲ ንያንታከይ የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር(ካፍ) ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ምክር ቤት አባል እንደሆኑ መሆናቸው ተነግሯል።

የጋና እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ከሆኑ ጀምሮ የሙስናን አስከፊነት በተመለከተ በርካታ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ መቆየታቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram