የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ45 ኢትዮጵያዊያን ምህረት አደረጉ

የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በተለያዩ ወንጀል ተከሰው በሀገሪቱ በእስር ላይ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ምህረት አደረጉ።

በዛሬው እለት ምህረት የተደረገላቸው ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ከ1 እሰከ 10 ዓመት ተፈርዶባቸው በጅቡቲ ማረሚያ ቤት የነበሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ ምህረቱን ያደረጉት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቅርቡ በጅቡቲ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ እና የረማዳን በዓል ምክንያት በማድረግ መሆኑም ተገልጿል።

በጅቡቲ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በይቅርታ የተፈቱትን ኢትዮጵያዊያንን ተቀብሎ እያስተናገዳቸው ሲሆን፥ አስፈላጊው የጉዞ ሰነድ ተዘገጅቶላቸው በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱም ተገልጿል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤምባሲው አማካኝነት ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይና የፍትህ ሚኒስቴሮች ጋር ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram