fbpx
AMHARIC

የድሬዳዋና መቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አገናኝ መንገዶች ግንባታ እየተካሄደ ነው

የድሬዳዋ እና መቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አገናኝ መንገዶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ በቅርቡ ግንባታቸው የተጀመረው አገናኝ መንገዶች 26 ኪሎ ሜትር ርዝመት አላቸው።

ለመንገዶቹ ግንባታ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል ብለዋል የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ።

በቀጣይም የአዳማ፣ ደብረ ብርሃን፣ አረርቲ እና ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አገናኝ መንገዶች ግንባታ እንደሚጀመር ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።

ጥናቱ ሲጠናቀቅም 47 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑትን የአራት ኢንዱስትሪ ፓርኮች አገናኝ መንገዶች ግንባታ ለመጀመር ጨረታ ይወጣል ብለዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram