የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጄብ ሴሺንስ የኤፍ ቢ አይ የቀድሞ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩትንና አሁን ላይ በቢሮው በሀላፊነት ሲሰሩ የነበሩትን አንድሪው ማክኬቢን አባረሩ።
ማክኬቢ በተደጋጋሚ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አድልዎ ይፈፅማሉ ተብለው ወቀሳ ሲነሳባቸው ነበር።
ባለፈው ጥር ወር ማክኬቢ ከስልጣናቸው ዝቅ በማለት ምክትል ዳይሬከተር መሆናቸው ይታወሳል።
ተሰናባቹ ባለስልጣን ኤፍ.ቢ.አይ በሂላሪ ኪሊንተን የኢሜይል አጠቃቀም እና በአሜሪካ ምርጫ የሩሲያ ጣልቃ ገብነት ላይ ሲያደርግ በነበረው ምርመራ ላይ ሲሳተፉ ነበር።
ባለስልጣኑ 50ኛ የልደት በአላቸውን ለማክበር 2 ቀናት ሲቀራቸውና የጡረታ መብታቸውን አስከብረው ስልጣን ለማስረከብ ቀናት ሲሯቸው ነው የተባረሩት።
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ጄብ ሴሽን ማክኬቢ በተደረገባቸው ምርመራ አድሎ ሲፈፅሙ እንደነበር በመታወቁ ምክንያት መባረራቸውን ነው ያስታወቁት።
ምንጭ:- ቢቢሲ
Share your thoughts on this post