ከሰሞኑ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች አለመረጋጋት መከሰቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የኢፊዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጥላዮ ጌቴ ለአማራ ቴሌቪዥን እንዳስታወቁት የተቀመጠው የመግቢያ የጊዜ ገደብ ችግሩ እስኪፈታ ለተማሪዎች ደህንነት ከማሰብ የመጣ ጊዜያዊ መፍትሄ ነው፡፡ቆይተውም ጊዜያዊ ነው ብለዋል፡፡
ዶክተር ጥላየ እንዳሉት የተማሪዎችን ደህንነትን ለመጠበቅ ሲባል ማንኛውም ተማሪ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የመከውነውን ማህበራዊ ጉዳይ አጠናቆ በማደሪያ ክፍሉ መገኘት አለበት፡፡
ተማሪዎቹ ለአደጋ እየተጋለጡ ያሉት በምሽት ስለሆነ በጊዜ ወደ መኖሪያቸው እንዲገቡና ከአደጋ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ነው፡፡ወደ ቀደመ ሰላማቸው ሲመለሱ ደግሞ ይነሳል ብለዋል፡፡
ዶክተር ጥላየ በአለመረጋጋቱ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ የተማሪ ቤተሰቦች ፣ጓደኞቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ያደረጉ ወንጀለኞች በስር ቁጥጥር እንዲውሉ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡
Share your thoughts on this post