fbpx

የዛሪማ ሜይዴይ ግድብ ግንባታ ከ87 በመቶ በላይ ደረሰ

የዛሪማ ሜይዴይ ግድብ ግንባታ በ2010 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀሙ 87 ነጥብ 99 መድረሱ ተገለፀ።

የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ፥ ግንባታውን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ወደ 95 ነጥብ 93 በመቶ ለማድረስ የተለያዩ የግድቡ ክፍሎች በግንባታ ላይ ይገኛሉ።

በግንባታ ላይ ከሚገኙት ውስጥም የዋናው ግድብ፣ የውሃ ማስተንፈሻ፣ የውሃ ማስወጭያ ዋሻ፣ የውሃ ማስወጫ ማማ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል አቶ ብዙነህ።

ግድቡ 805 ሜትር ርዝመት፣ 152 ሜትር ከፍታ እና 3 ነጥብ 497 ቢሊየን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ነው።

በፕሮጀክቱ አንድ የግንባታ ሥራ ተቋራጭና አንድ የቁጥጥር አማካሪ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፥ 929 ዜጎች የስራ እድል አግኝተዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 242 ሴቶች ናቸው።
አጠቃላይ የፕሮጀክቱ በጀት 15 ቢሊዮን ብር ነው።

የዛሪማ ሜይዴይ ግድብ በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራባዊ ዞን ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram