የዓለም ጤና ድርጅት በኮንጎ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ፡፡

እስከአሁን በበሽታው 44 ሰዎች መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን 23ቱ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡ የበሽታ ስርጭቱ ከገጠር ወደ ከተማ በመስፋፋት ላይ ይገኛል፤ አንድ ሚሊየን በሚኖርባት ምባንዳካ ከተማም የበሽታው ምልክት የታየበት አንድ ግለሰብም ተገኝቷል፡፡

ድርጅቱ ከ 44ቱ ግለሰቦች መካከል ሦስቱ በሽታው እንዳለባቸው የተረጋገጠ ሲሆን፥ 20ዎቹ የበሽታው ምልክት ታይቶባቸዋል እንዲሁም የ 21 ግለሰቦች ሁኔታ ደግሞ ገና አለየለትም ተብሏል፡፡ የጤና ባለሙያዎች እስከአሁን ከሰዎቹ ጋር ንክኪ አደርገዋል ያሉዋቸውን 433 የሚደርሱ ግለሰቦችን ተለይተዋል፤ ከ 4 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ለመለየት ጥረታ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

የድርጅቱ የአደጋ ጊዜ ምክትል ዳይሬክተር ሳላማ በኮንጎ ወንዝ አካባቢ የታየው የበሽታው ምልክት ወደ ኮንጎ ብራዛቪልና ወደ መካከለኛው አፍሪካ ሊስፋፋ እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ክትባቱ ከኔጌቲቭ 60 እስከ ኔጌቲቭ 80 በሆነ ማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ ያለበት ሲሆን፥ በኮንጎ ያለው የኤሌክትሪክ ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram