fbpx

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ደም ለገሱ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በመስቀል አደባባይ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት ለደረሰባቸውን ዜጎች በዛሬው እለት ደም ለግሰዋል።

ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በመስቀል አደባባዩ የቦምብ ፍንዳታ ጎዳት የደረሰባቸውን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተኝተው ህክምና በመከታተል ያሉ ዜጎችንም ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላም ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በመስቀል አደባባዩ የቦምብ ፍንዳታ ጎዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ደም ለግሰዋል።

ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ፥ ሰኔ 16 2010 ዓ.ም እየመጡ ያሉ ለውጦችን ለማበረታታት በወጡ ዜጎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልፀዋል።

በቦብም ጥቃቱ ጉዳት የተደረሰባቸው እና ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ለፍቅር፣ ለሰላም እና ለአንድነት መሰዋእትነት የከፈሉ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

ይህን መሰል እኩይ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት አለም ላይ ያሉ አሸባሪዎች ሳይሆኑ እኛው ውስጥ ያሉ መሆናቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡

የቦንቡ ፍንዳታ ጥቂት ግለሰቦችን ይጎዳል እንጂ የሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የለውጥ ፍላጉት ሊገታ አይችልም ብለዋል፡፡

የተሻለችውን ኢትዮጵያ ማየት ሁላችንም እንመኛለን ያሉት አቶ ለማ ምኞት ብቻ ሳይሆን በትጋት መስራትን ይጠይቃል ለዚህም እያንዳንድ ኢትዮጵያዊ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ብለዋል።

የተቃጣው ጥቃት የኋሊት የሚመልሰን ሳይሆን በእልህ እንድንሰራ የሚያደርገን ነው፤ ለውጥ ሁሉ ዋጋ ያስከፍላል ወደ ፊትም በአንድነት ተባብረን መቀጠል አለብን ብለዋል።

ስንተባበር የችግር እድሜ ያጥራል አንድነታችንን በጓዳ ሳይሆን በአደባባይ በመታገል የምንመኛትን ኢትዮጵያ መፍጠር ይጠበቅብናል ብለዋል።

ርእሰ መስተዳደሩ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ባለሞያዎችን ላደረጉት ትብብር እና የዜጎች ህይወት ማትረፍ ተግባር አመስግነዋል።

በሰርከካለም ጌታቸው

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram