fbpx

የኤች አይ ቪ ቫይረስ ክትባት የምርምር ውጤት ተስፋ ሰጪ ሆኖ ተገኝቷል- ተማራማሪዎች

የኤች አይ ቪ ቫይረስ ክትባት ላይ አየተደረገ ያለው ምርምር ውጤት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ተመራማሪዎች ገለጹ።

የቦስተን ተመራማሪዎች እድሜያቸው ለአቅመ ሄዋንና አዳም በደረሱ ጤናማ ሰዎችና ጦጣዎች ላይ በአደረጉት ምርምር ክትባቱ የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ማድረግ ችሏል ነው የተበላው።

ጥናቱ ከተካሄደባቸው ጦጣዎች መካከል ሁለት ሶስተኛ ያህሉ ከኤች አይቪ ባይረስ ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው ቫይረሶች መካላከል መቻሉም ነው በጥናቱ የተመላከተው።

ክትባቱ ለ400 ጤናማ ሰዎች የተሰጠ ሲሆን፥ ክትባቱ ከተሰጣቸው 5 ሰዎች አንዱ ላይ የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅም በመጨመር ውጤታማ መሆኑ ታውቋል።

ወደፊትም ለቫይረሱ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ለሆኑ 2 ሺህ600 ያህል የደቡብ አፍሪካ እናቶች ክትባቱን ለማስጠት ታቅዷል ተብሏል።

በዚሁ ጥናት ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘ ቢሆንም ምንጊዜም በእንሰሳትና ሰዎች መካከል ተመሳሳይ ውጤት ሊገኝ እንደማይቻልና የጥናቱን ውጤት ለመግለጽ ጥንቃቄ የሚያስፈልግ መሆኑን የጥናቱ መሪ ዶ/ር ዳን ባሩች ተናግረዋል።

የሰውነትን ከኤች አይቪ ቫይረስ የመከላከል አቅምን የሚያሳድግ ክትባት ተገኘ ማለት ሙሉ በሙሉ ቫይረሱን መቆጣጠር መቻል ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ባሩች አስረድተዋል።

ጥናቱ አሁን ላይ እየተሰራ ካለው የቫይረሱን ቁጥጥርና ህክምና ጋር ተዳምሮ የስርጭቱን ፍጥነት ሊገታ ይችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ነው ተብሏል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን ላይ 38 ሚሊየን ያህል ህዝብ ከቫይረሱ ጋር ይኖራል፤ በየዓመቱም 1.8 ያህል ሰዎች በቫይረሱ እንደሚበከሉ ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

 

 

ምንጭ፦ upi.com

የተተረጎመው፦ በእንቻለው ታደሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram