fbpx

የኤርትራና የኢትዮጵያን የሰላም ግንኙነት ለረጅም ጊዜ ስንፈልገው የነበረ ነው – የሃይማኖት መሪዎች

የኤርትራና የኢትዮጵያን የሰላም ግንኙነትን ለረጅም ጊዜ ሲፈልጉት የነበረ መሆኑን የሃይማኖት መሪዎች ገለጹ።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፉት መቶ ቀናትም ሰላምን እንዲሰፍ፤ በይቅርታና በፍቅር ዜጎች ተሳስበው እንዲኖሩ በማድረግና ህዝቡ በማዳመጥ በርካታ ተግባራትን ማከናዎናቸውን የኢትዮጵያ ኢርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዑ ወቅዱ አቡነ ማቲያስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮፖሬት ገልጸዋል።

ይህ ቀን እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያናችን ስትፈለገው ብቻ ሳይሆን ፈጣሪ በፀሎት ስትጠይቅ ቆይታለች ሲሉም አስረድተዋል።

የተጀመረውን ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምዕመናኑ የለውጡን እንዲያግዙም ቤተክርስቲያኗ የሚጠበቅባትን አስተዋጽኦ ማበርከቷን እንደምትቀጥልም ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሀጂ አልፋድ አሊ ሙስጠፋ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዜጎች በአንድነት ለሃገራቸው አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እየተከተሉ ያለው መንገድ ውጤታማ መሆኑን አስረድተዋል።

ለዚህም ከ20 ዓመት በላይ ከኤርትራ ጋር የነበረውን የጥርጣሬና የጠላት ገመድ በመበጠስ በፍቅር ስንሰለት ያስተሳሰሩ ሲሆን፥ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከሁለቱ ሀገር እህትና ወንድማማች ህዝቦች ጋር የሃይማኖት መሪዎች መስራት እንዳለባቸው ነው ሀጂ አልፋድ አሊ ሙስጠፋ የተናገሩት።

ህብረ ብሄራዊነት ያገናዘበ የአመላካከት ልዩነቶች እንዲስተናገዱ ጠ/ ሚኒስትሩ የወሰዷቸው የእርምት አርምጃዎችም ሰፊ መሆቸውንም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ቤተ ክርስቲያን ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ አስረድየዋል።

ዜጎች በየትኛውም የአለም ከፍል ቢሆኑ በኢትዮጵያዊነታቸው እንዲኮሩ የሚያደረግ ተግባርም ከመሪያቸው ዶ/ር አብይ አህመድ ባለፉት 100 ቀናት አግኝተዋል ብለዋል።

ከባለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ገብታ እንደነበር የሚያስታውሱት የኢትዮጵያ ወንጌላዊያ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ፃዲቁ አብዶ ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ጠ/ ሚኒስትርነት መምጣትን ተከትሎ የስጋት ደመናው ተኗል ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ አብይ ቀድመው የተካማቹ ችግሮችን መፍታት ብቻ ሳይሆን አዲዲስ ሁኔታቸውን በአስተሳሰብ እና በተግባር የቀየሩ መሆናቸውንም አመላክተዋል።

ዶ/ር አብይ አህመድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳዩትን የለውጥ ተምሳሌት ዜጎች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅና የተሻለ ስራ በማከናውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በላይ ተስፋዬ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram