fbpx

የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የአበጠር ወርቁ የህክምና ወጭ እንዲሸፈን ትዕዛዝ ሰጠ

ህፃን አበጠር ወርቁ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል እየተረዳ ሲሆን፣የጤናው ሁኔታ አንፃራዊ መሻሻል እንዳሳየ አስታማሚው አቶ ሙጨ ደጀን ተናግረዋል፡፡

የህፃኑ አይን በህክምና ሊፈወስ እንደሚችል ሃኪሞች ተናግረዋል፡፡ የደም ማነስ ገጥሞት ደም እየተሰጠውም ይገኛል፡፡

የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አበጠር እንዲረዳ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን የአቤት እና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሀላፊነት ተሰጧቸዋል፡፡

የአቤት ሆስፒታል ሚዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አያሌው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት አበጠርን ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡የሚያስፈልጉትን የህክምና መሳሪያዎችን እያሟላንም ነው ብለዋል፡፡

ህፃን አበጠር ወርቁ የፈለገህይዎት ህክምናውን ጨርሶ ወደ አዲስ አበባ ለተሻለ ህክምና የሚሄድ ይሆናል፡፡

በህፃን አበጠር ወርቁ ላይ የአካል ማጉደል ካደረሱ ተጠርጣሪዎች መካከል ሶስቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአስነዋሪ ድርጊቱ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል ሁለቱ ባለፈው ዓርብ ከዲባጢ ወረዳ ሸሽተው ቡለን ወረዳ ላይ እንደተያዙ የዲባጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ በልጋፎ ተናግረዋል፡፡

ዞኑም ጎጂ ባህላዊ ድርጊቱን ለማጥፋት እየሰራ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል፡፡

በየሺሀሳብ አበራ – አብመድ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram