የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሰሞኑ የት ናቸው? ፕሮግራማቸውን እነሆ

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት በሶማሌ ክልል የመጀመሪያውን የስራ ጉብኝትና ከክልሉ ነዋሪዎች ጋርም ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር በዚሁ በመቀጠል በዚህ ሳምንትና በቀጣዩ ሳምንት የተለያዩ ህዝባዊ መድረኮችን ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ታውቋል።
በዚህም መሰረት…
 ረቡዕ (ሚያዚያ 3) በአምቦ ከተማ ከአምቦ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፤
 ሀሙስ (ሚያዚያ 4) በአገር ውስጥ ካሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ይወያያሉ፤
 አርብ (ሚያዚያ 5) በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ከህዝቡ ጋር ይወያያሉ፤
 እሁድ (ሚያዚያ 7) በአዲስ አበባ ሚሌኒየም አዳራሽ ከመላ አገሪቷ ከተወጣጡ ከ25 ሺ በላይ ወጣቶች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፤
 ሰኞ (ሚያዚያ 8) በሸራተን አዲስ ከባለሀብቶች ጋር ውይይት ይኖራቸዋል።


ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram