fbpx

የኢንተርኔት ሱስ እና የጤና መዘዙ

መረጃ ፍለጋ ወይም የራቀ ወዳጅ ዘመድዎን በአካል ያገኙት ያክል እንዲሰማዎት ኢንተርኔትን እንደ አማራጭ ይጠቀማሉ።

ምናልባትም በቀናት ልዩነት የሚያደርጉት ከሆነ መልካም ነው ፤ ይህ ልማድ ሲበዛና ወደ ከፍተኛ ሱስ ሲቀየር ግን ለጤናዎ ጠንቅ ይሆናል።

ኢንተርኔትን አብዝቶ መጠቀም የሚያመጣውን የጤና እክል በመረጃ ለማስደገፍ በተደረጉ ጥናቶችም፥ አብዝተው የሚጠቀሙት ሰዎች በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ እና ለተለያዩ የጤና እክሎች ተጋላጮች መሆናቸው ታይቷል።

በጥናቱም አብዝተው ኢንተርኔትን የሚጠቀሙት ከማይጠቀሙት ይልቅ ለጉንፋን እና ኢንፍሉዌንዛ በሽታዎች በ30 በመቶ የበለጠ የመያዝ እድላቸው ሰፊ ነው።

በዌልሷ የስዋንሲ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ፊል ሪድ እንድሚሉትም ፥ ድብርት ፣ የእንቅልፍ እጦት እና ብቸኝነት ከከፍተኛ ኢንተርኔት ተጠቃሚነት እና ከጤና እክል ጋር የተያያዙ ናቸው።

በዚህ ጥናት መሰረት እነዚህ ኢንተርኔትን አብዝተው የሚጠቀሙ ሰዎች ፥ የሚያገኙትን አገልግሎት ሲያቋርጡ ለከፍተኛ ጭንቀት ይጋለጣሉ።

ይህ ጭንቀት ደግሞ ሰውነት በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጣና በቀላሉ ለበሽታ ተጋላጭ እንዲሆን ያደርገዋል።

ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች ደግሞ የኢንተርኔት ሱሰኞች ለእንቅልፍ እጦት፣ ለተዛባ የአመጋገብ ስርአት እንዲሁም ለሲጋራ እና ለከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ሱስ ተጋላጭ መሆናቸውን ያሳያሉ።

ታዲያ እነዚህ ሁሉ የኢንተርኔት ሱሶች ማረፊያቸው የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ማሳጣትና ተጠቃሚዎችን ደግሞ ለተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ ማጋለጥና ከፍተኛ የጤና እክሎችን መፍጠር ነው።

ለመረጃ፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር ለመገናኘት እና ለመዝናኛ ብለው የሚጀምሩት የኢንተርኔት ሱስ ሲታሰብ የማይመስል የጤና ችግር አለውና ልብ ብለው ያስቡበት።

ልብ ይበሉ የሚከሰተው የጤና እክል ኢንተርኔትን ከመጠን በላይ አብዝተው በሚጠቀሙ እንጅ ለስራ ጉዳይ እና መጠነኛ አገልግሎት የሚያገኙትን አያካትትም ሁሉንም በልኩ ያደረጉ የፈለጉትን በጊዜ ያገኛሉና።

ምንጭ ፥ www.swansea.ac.uk

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram