fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች በታንዛኒያ የ3ዓመት እሥር ተፈረደባቸው

የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላለፈ። ኢትዮጵያዊያኑ የተያዙት በታንዝኒያ ማዕከላዊ ክፍል “ኢሪንጋ” በሚባል ቦታ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ሊያልፉ ሲሉ ነው -በታንዛኒያ ፖሊስና በሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የተያዙት።

ኢትዮጵያዊያኑን በታፈነ መኪና አጉሮ ሲያጓጉዟቸዉ የነበረ ሾፌር ሲያመልጥ ፖሊስ ከፍልሰተኞቹ ጋር የነበረ ሐሰን ፌሩዝ የሚባል ታንዛኒያዊን በቁጥጥር አውሎታል።

ሆፕ ካዋዋ በታንዛኒያ የኢሪንጋ ግዛት ኢሚግሬሽን ኃላፊ

“ኢትዮጵያዊያኑን በቁጥጥር ሥር ስናውላቸዉ ከ84ቱ ውስጥ 12ቱ ራሳቸውን ስተዉ ስለ ነበር፤ ወደ ኢሪንጋ ሆስፒታል ተወስዶ ህክምና እንዲደረግላቸው ተደርጓል” ሲሉ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በታንዛኒያ ኢምባሲ የሌላት ሲሆን የአሜርካ ድምፁ ጉዳዩ የሚመለከተውን ኬንያ ያለውን የኢትዮጵያን ኢምባሲ ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። VOA Amharic

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram