fbpx

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ምርጫ ግንቦት 26 ይካሄዳል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዝዳንትና የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ግንቦት 26 ቀን 2010 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ እና ስራ አስፈፃሚዎች እጩዎች እስከ ባለፈው ቅዳሜ ድረስ ለምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ መግባታቸው ይታወሳል።

በዚህም መሰረት፦

አቶ ኢሳያስ ጂራ – ኦሮሚያ

አቶ ተስፋዬ ካህሳይ – ትግራይ

ኢንጂነር ቾል ቤይል – ጋምቤላ

አቶ ተካ አስፋው – አማራ

ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ – አዲስ አበባ

አቶ ጁነይዲ ባሻ – ድሬዳዋ ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንትነት ቀርበው ነበር።

ሆኖም ግን ለፕሬዝዳንትነት እጩ ከሆኑ 6 ግለሰቦች መካከል የትግራይ ክልል እጩ አድርጎ የወከላቸው አቶ ተስፋዬ ካህሳይን ውክልና ማንሳቱን በደብዳቤ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የደቡብ ክልልን በመወከል በእጩነት ቀርበው የነበሩት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስም ለፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንትነት ተፎካካሪ ሆነው ከቀረቡ ግለሰቦች መካከል

የሚጠቀሱ ቢሆንም አርብ ዕለት በምርጫው እንደማይወዳደሩ ታውቋል።

ዶክተር አሸብር በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጠጡት መግለጫም፥ በምርጫው አስቀድሞ የመወዳደር ፍላጎት እንዳልነበራቸው ጠቁመውዋል።

“ደቡብ ክልል ወክሎኝ ተወዳዳሪ ነበርኩ፤ ከጅምሩም እውነቱን ለመናገር ብዙም ፍቃደኛ አልነበርኩም፤ ግን በተደጋጋሚ በቀረበው ጥሪ ገባሁ፤ ሆኖም ግን በምርጫው ሂደት ለስፖርቱ የማይበጅ ብዙ ነገሮች በመከሰታቸው ራሴን ከውድድሩ አግልያለሁ” ብለዋል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፕሬዚዳንትና የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ግንቦት 26 ቀን 2010 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram