fbpx

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ ምርጫ ነገ ይካሄዳል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን የፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ነገ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዩ አራት 4 የሚመሩት ፕሬዚዳንት እና ስራ አፈጻሚ አባላትን ለመምረጥ ከመስከረም 30 ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይደረግ መቆይቱ ይታወሳል።

ሆኖም ግን ፊፋ ምርጫው በአስቸኳይ እንዲካሄድ አስገደጅ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ምርጫው ነገ ግንቦት 26 በአፋር ክልል ሰመራ ሊደረግ የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለታል።

በነገው እለት በሚካሄደው ምርጫ ላይም አራት እጩዎች ለፕሬዚዳንትነት ፤ 22 እጩዎች ደግሞ ለስራ አስፈፃሚነት ይወዳደራሉ።

ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩትም፥

አቶ ጁኔይዲ ባሻ ቲልሞ- ከድሬ ዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ተካ አስፋው ተሰማ – ከአማራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ኢሳያስ ጅራ ባሻ – ከኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ተስፋዬ ካህሳይ ገብረእግዚአብሄር- ከትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ተስፋዬ ካህሳይ የትግራይ ክልል ውክልናውን በማንሳቱ ከውድድር ውጭ ተደርገው የነበረ ሲሆን፥ የፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ግን ከምርጫው ውጪ እንዲሆኑ አቶ ተስፋዬ ካህሳይ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ መሻሩን አስታውቀዋል።

የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ይህንን ያደረገውም በግለሰቡ እና በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መሀከል የወካይ እና ተወካይ ግንኙነት ባለመኖሩና የቃለ ጉባኤ ጉዳይም በእግር ኳስ መተዳደሪያ ደንቡ ላይ ያልሰፈረ መስፈርት በመሆኑ እንደሆነ አብራርተዋል።

በነገው እለት በኪካሄደው ምርጫ ላይ 22 እጩዎች ለስራ አስፈፃሚነት ይወዳደራሉ።

እነዚህም፦

አቶ አበበ ጋላጋይ ዘለቀ – ከድሬ ዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ አራጋው – ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ አሊሜራህ መሃመድ አሊ- ከአፋር እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ሆርሳ – ከደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ሰውነት ቢሻው ውቤ – ከአማራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ አብዱራዛቅ ሀሰን መሃመድ – ከኢትዮጵያ ሶማሌ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ከማል ሁሴን መሃመድ – ከኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ አስራት ሀይሌ ገብሬ – ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ኮሎኔል አወል አብዱራሃም ኢብራሂም- ከትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ዶክተር ሲራክ ኃይለማርያም ከለለው – ከአማራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ወንዳወክ አበዜ ወርቁ – ከድሬ ዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ኡቻላ ኦጁሉ ኦቦንግ – ከጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን በባከር -ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ኢብራሂም መሃመድ ኢብራሂም- ከሐረሪ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ወልደ ገብርኤል መዝገቡ ተስፋዬ – ከትግራል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ኢንጂነር ሀይለኢየሱስ ፍሰሀ አለማየሁ – ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ሙራድ አብዲ ሀቢብ – ከሐረሪ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ ፋንታዬ – ከአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ዶክተር ቻን ጋቶክ ዮም – ከጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ ኪዳኔ – ከድሬ ዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አቶ ዳግም አስመላሽ – ከጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ዶክተር ሀይሌ ኢቲቻ ቡልቱ – ከኦሮሚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ሰመራ ከተማም እሁድ ግንቦት 26 2010 ዓ.ም የሚደረገውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን የፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅቷን አጠናቃ በመጠባበቅ ላይ ነች።

በሙለታ መንገሻ(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram