fbpx

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 100ኛ አውሮፕላኑን ሊረከብ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን የአውሮፕላኖችን ብዛት መቶ በማድረስ ከአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

አየር መንገዱ የፊታችን ግንቦት 28 የሚረከበው ቦይንግ 787-900 አውሮፕላን ለአየር መንገዱ 100ኛ አውሮፕላኑን በመረከብ አዲስ ታሪክ የሚያስመዘግብ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እንዳሉት አየር መንገዱ 100ኛ አውሮፕላኑን ሲረከብ ለኢትዮጵያዊያን ኩራት ነው፡፡

ይህም አየር መንገዱ በአፍሪካ በዘርፉ እየተጫወተ ያለውን የመሪነት ሚና ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ከአምስት ዓመት እድሜ የማይበልጡት እነዚህ 100 አውሮፕላኖች እጅግ ዘመናዊ እንደሆኑም ተመልክቷል፡፡

አየር መንገዱ በአምስቱም አህጉሮች በሚሰጠው አገልግሎት ከ110 የሚልቁ አለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram