fbpx
AMHARIC

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑን በመጪው ሰኞ ይረከባል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ዘማናዊ እና የመጀመሪያ የሆነውን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በመጪው ሰኞ እንደሚከረከብ አስታወቀ።

በደማቅ ሁኔታ ሰኞ ዕለት በሚካሄደው የርክክብ ስነ ስርዓት የአየር መንገዱ የስራ ሀላፊዎች ፣ ታዋቂ ሰዎች እና የቦይንግ ኩባንያ ተወካዮች በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በመጪው ሰኞ አዲስ አበባ የሚገባው አዲሱ አውሮፕላን የመገጣጠምና በአየር መንገዱ አርማዎች  የማስዋብ ስራ ተጠናቋዋል።

አየር መንገዱ ዘመናዊ አውሮፕላኑን ከቦይንግ ኩባንያ ከመረከቡ አንድ ቀን ቀድሞ በአውሮፓ 13ኛውን በስፔን ሁለተኛ የሆነውን በረራ ወደ ባርሴሎና እንደሚጀምር ታውቋል።

አየር መንገዱ ከአፍሪካ የመጀመሪያ የ100 አውሮፕላኖች ባለቤት ያደረገውን ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን በቅርቡ ተረክቦ 12ኛ የአውሮፓ መዳረሻ ወደ ሆነችው ጄኔቭ በረራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

በቅርቡ የሚረከበው አውሮፕላን በፈረንጆቹ 2025 በአውሮፕላን ቁጥር የያዘውን እቅድ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነግሯል።

አፍሪካን በንግድ ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም ለማስተሳሰር የአየር መንገዱ ትኩረት እየራ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ይህን ለማጠናከርም ተጨማሪ አምስት ቦይንግ 787 እና 16 ኤር ባስ ኤ 350 አውሮፕላኖችን እንዳዘዘ ከዚህ በፊት አሰታውቆ።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram