የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአዋሽ ሰባት ኪሎ በ180 ሚሊዮን ብር ያስገነባው ነዳጅ ማከፋፈያ ዴፖ አስመረቀ

ድርጅቱ በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ቅጥር ግቢ ውስጥ በ 180 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን ነዳጅ ማከፋፈያ ዴፖ አስመርቋል፡፡

የነዳጅ ማከፋፈያ ዴፖው በቀን ለ250 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች መጫን የሚችል ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀይለማርያም አዲሱ ዴፖ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ነዳጅን ከማከማቸት ባለፈ የማከፋፈል አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል፡፡

የነዳጅ ዴፖው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተገነባ ሲሆን አውቶማቲክ የእሳት ማጥፊያን ጨምሮ ዘመናዊ የነዳጅ መጫኛ መሳሪያዎች ተገጥመውለታል፡፡

በየአመቱ በ 10 በመቶ የሚያድገውን የሀገሪቱን የነዳጅ ፍላጎት ለማሟላትም የነዳጅ ዴፖው እገዛ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የቦርድ አባል አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች 13 የመጠባበቂያ ነዳጅ ማከማቻ ዴፖዎች አሉት

ሪፖርተር:-ጌታቸው ባልቻ

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram