fbpx

የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ ሁለት ህዝብ ነው ብለው የሚገልፁ ሀቁን የማያውቁ ብቻ ናቸው- ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድራን፣ ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የጥበብ ሰዎች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በብሄራዊ ቤተመንግስት በተደረገላቸው የምሳ ግብዣ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ ለሰላም ያለው ፍላጎት እና ምኞች መግለፁን አንስተዋል።

በዚህም “የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ከእንግዲህ ሁለት ህዝቦች ናቸው ብለው የሚገልፁ አካላት ካሉ ሀቁን የማያውቁ ናቸው” ብለዋል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በባህል፣ ወግና ቋንቋ የተሳሰረ አንድ ታሪክ ያለው እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

በቀጣይም የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች በጋራ እንደሚሰሩና ለሌሎች የአለም ህዝቦች አርዕያ የሆነ ተግባር እንደሚፈፅሙ ገልጸዋል።

ይህን የህዝቦች መቀራረብና መተባበር ሳያዩ ህይወታቸውን ላጡ ማዘነቸው የገለፁ ፕሬዚዳንቱ፥ በግላቸው ይህን ለማየት በመቻላቸው ደስተኛ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

በሂደትም የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች በመካስ ተቀራርበውና ጠንክረው እንዲሰሩ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው፥ የአዲስ ኣበባና አከባቢዋ ህዝብ ዛሬ ጠዋት የልኡካን ቡዱኑ በሚያልፉባቸው አውራ ጎዳናዎች ዳርና ዳር በመሆን ላደረጉት ደማቅ አቀባበልና ላሳዩት ፍቅር ምስጋና አቅርባዋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram