fbpx

የአፕል አሴት 1 ትሪሊየን ዶላር ደረሰ

አፕል የ1 ትሪሊየን አሴት ሲያዝመዘግብ በአሜሪካ የህዝብ ኩባንያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ነው ተብሎለታል፡፡

ሆኖም አፕል ትሪሊየን ዶላርን ሲሻገር በዓለም የመጀመሪያው አይደልም የተባለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በነዳጅ ዘርፍ ላይ የተሰማራው በአሁኑ ወቅት ዋጋው ያሽቆለቆለበት ፔትሮቻይና ቀዳሚ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የአፕል ኩባንያ እዚህ አሴት ላይ ለመድረስ የበቃው ሐሙስ በዋለው የአክስዮን ሽያጭ ለአንድ አክስዮን ከ207 ነጥብ 04 ዶላር በላይ ማስመዝገብ በመቻሉ ነው ተብሏል፡፡

ለኩባንያው አሴት መጨመር አዳዲስ ምርቶቹ የሆኑት አይፎን ስምንት እና አይፎን ኤክስ ጉልህ አስተዋፅዖ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በእስያ አህጉር በተለይም በቻይናና በጃፓን ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ ሲሆን በተጨማሪም በቴክኖሎጂ ላይ የተሰማሩ ኢንቨስተሮችም ትልቅ አስተዋፅዖ አድርገዋል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ሌሎቹም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዚህ ዓመት ዕድገት ማሳየታቸው የተገለጸ ሲሆን በአሴትም አፕል ኩባንያን እየተከተሉት ነው ተብሏል፡፡

አማዞን 900 ቢሊየን ዶላር አሴት ላይ ደርሷል፤ እንዲሁም ጎግልና ማይክሮሶፍት ከ800 ቢሊየን ዶላር በላይ አስመዝግበዋል፡፡

 

ምንጭ፦ሲኤንኤን
አብርሃም ፈቀደ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram