fbpx
AMHARIC

የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች እጅግ ፈጣን የሆነውን የኳንተም ኮምፒውተር ባለቤት ለመሆን ተቃርበዋል

በ ሚሼል ሲሞን የሚመራው የአውስትራሊያ የዘርፉ ተመራማሪዎች ቡድን እጅግ አመርቂ የሚባሉ ርምጃዎችን በኳንተም ኮምፒውተር ዘርፍ ማምጣታቸው እየተነገረ ነው፡፡ ሲሞን እና ቡድኗም ትላንትና ረቡእ እለት የኳንተምቢት (quantum bits) ከነጠላ የፎስፈረስ አተም በሲልከን ውስጥ መገንባታቸውን አሳውቀዋል፡፡

ይህ የተፈጠረው አተም የተግባቦት ስርዓት መፍጠሩን እና እርስ በራሱ መዛመዱን ተነግሯል፡፡

የኳንተም ኮምፒውተር የሳይንስ ዘርፍ አሁን ግልጋሎት እየሰጠ ያለውን የባለ 0 እና 1 ቢት ኮምፒውተር የመጨረሻ ትንሹ በሆነ ፓርቲክል ይተካል ተብሎ የሚታሰብ ኮምፒውተር ነው፡፡

የኳንተም ኮምፒውተሩ እውን ሲሆን በሽህ እጥፍ ከአሁኖቹ ከምፒውተሮች በፍጥነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ስራዎችን መከወን የሚያስችል ሲሆን በስራ ያሉ ኮምፒውተሮች ችግሮችን ለመፍታት ሺ አመታት የሚጠይቁትን በደቂቃዎች ውስጥ መፍትሄ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡


ምንጭ፡- ዘጋርዲያን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram