fbpx

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጆርካ ኢቨንትስ ስያሜውንና መለያውን በመጠቀም የሚለቃቸው ማስታወቂያዎች ህገ ወጥ መሆናቸውን ገለጸ

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በሃገር ውስጥ የተለያዩ ሁነቶችን የሚያዘጋጀው ጆርካ ኢቨንትስ የቻምፒየንስ ሊጉን ስያሜና መለያ በመጠቀም የሚለቃቸው ማስታወቂያዎች ህገ ወጥ መሆናቸውን ገለጸ።

የቻምፒየንስ ሊጉ የቴሌቪዥን ሁነት እና ሚዲያ ገበያ ክፍል ለጣቢያችን በላከው መግለጫ፥ ጆርካ ኢቨንትስ ከቻምፒየንስ ሊጉ የፍጻሜ ጨዋታ ጋር በተያያዘ የቻምፒየንስ ሊጉን ስያሜና መለያ መጠቀሙ አግባብነት የሌለውና ህገ ወጥ ነው ብሏል።

ጆርካ ኢቨንትስ በነገው እለት ፍጻሜውን የሚያገኘውን ቻምፒየንስ ሊግ፥ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ለማሳየት ዝግጅት ማጠናቀቁን በሚመለከት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ ሲያስነግር መቆየቱንም ገልጿል።

በዚህም ጆርካ ኢቨንትስ ለዝግጅቱ የቻምፒየንስ ሊጉን ስያሜና መለያ ላዘጋጀው የፍጻሜ ጨዋታ፥ በማስታወቂያነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት መጠቀሙን በመግለጽ ቅሬታውን አቅርቧል።

በመሆኑም ጆርካ ኢቨንትስ በማህበሩ ውክልና ያልተሰጠውና ህጋዊ የውክልና ፍቃድ የሌለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ላዘጋጀው ጨዋታ የቻምፒየንስ ሊጉን መለያም ሆነ ስያሜ መጠቀሙ አግባብነት የሌለው መሆኑንም ነው የገለጸው።

ድርጅቱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን የባለቤትነት መብት በሚጋፋ መልኩ እያስተላለፋቸው ያሉ ማስታወቂያዎችንም ሆነ የተሰቀሉ ትልልቅ ፖስተሮችን እንዲያስወግድ ጠይቋል።

ከዚህ ባለፈም ድርጅቱ የቻምፒየንስ ሊጉን ስያሜና መለያን ከራሱ ጋር እያዛመድ መጠቀም እንዲያቆምም ነው የጠየቀው።

በተጨማሪም ድርጅቱ የቻምፒየንስ ሊጉን ስያሜና መለያ ለማንኛውም ሁነትም ሆነ ዝግጅት ከመጠቀም እንዲታቀብም አስጠንቅቋል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram