የአውሮፓ ህብረት ከቀድሞው የሩሲያ ሰላይ መመረዝ ጋር በተያያዘ አምባሳደሩን ከሞስኮው ሊያስወጣ ነው
በሀገረ ብሪታኒያ ሩሲያ በቀድሞው የስለላ አባሏ ላይ በነርቭ ኬሚካል መርዛለች በማለት የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ምክር ቤት በሩሲያ ያለውን አምባሳደሩ ከመጥራት ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌለ በመስማማቱ ነው፡፡
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬሳ ሜይ በሀገራቸው ሩሲያ የፈፀመችው የነርቨ ጥቃት አውሮፓ ህብረትን ከመውረር የማይተናነስ ድርጊት ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡
ይሁን እንጂ ሩሲያ ድርጊቱን አለመፈፀሟን በመግለጽ ለነርቩ ጥቃቱ ሀላፊነት እንደማትወስድ አስታውቃለች፡፡
ባለፈው የካቲት 25 የነርቨ ኬሚካል ጥቃት የተፈፀመባቸው ሰርጌይ ስክሪፓል እና ልጁ ጁሊያ በአሁን ወቅት በአሳሳቢ የጤና ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡
የጋራ የደህንነት ስጋት በሆነው በዚህ ፈታኝ ወቅት ህብረቱ ከብሪታኒያ ጎን እንደሚሰለፍ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ገልጿል፡፡
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ሜይ የነርቭ ጥቃቱን ሩሲያ መፈፀሟን የሚያሳይ ማስረጃ ሲያቀርቡ ኬሚካሉን ሩሲያ በባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ እንዳመረተችው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Share your thoughts on this post