የአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ና የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልድያ የእግር ኳስ ክለብ ላይ የተጣለውን ቅጣት ተቃወሙ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልድያ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ላይ ያስተላለፈውን ኢፍትሀዊ የቅጣት ውሳኔ መሰርት በማድረግ በቢሮው የማህበራዊ ገፃችን ላይ ስናወግዝ መቆየታችን ይታወሳል ያሉት ሁለቱ አካላት፡፡

ዛሬም የወልድያ ከተማ ህዝብና ወጣቶች፤ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን፤ የአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮና መላው የክልላችን የስፖርት ቤተሰብ የተላለፈው ውሳኔ ፍትሀዊነት የጎደለውና የክልላችን ስፖርት እድገት ላይ ከፍተኛ ተፅኖ የሚያሳድር ድርጊት ነው በማለት አውግዘዋል ፡፡

ይህንንም መሠረት በማድረግ፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልድያ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ላይ ያስተላለፈውን ኢፍትሀዊ የቅጣት ውሳኔ መሰርት በማድረግ የአማራ ክልል እግ ኳስ ፌርዴሬሽንና የአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ በወልድያ ከተማ እግር ኳስ ከለብ ላይ ያስተላለፈውን ኢፍትሀዊ ቅጣት እንዲያስተካክል ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ ጥያቀቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፡-የአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ – Amhara National Regional State youth and Sport bureau

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram