fbpx

የአምባሳደሮች ጥሪ እና ሽግሽግ ተካሄደ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ምክንያቶች የአምባሳደሮች ጥሪ እና ሽግሽግ ማካሄዱን አስታወቀ።

በዚህም መሰረት አምባሳደር አሚን አቡድርቃድር ከሪያድ ወደ አልጄሪያ ተዛውረው ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው እንዲሰሩ ተመድበዋል።

አምባሳደር ውብሸት ደምሴ ከጅዳ ቆንስላ ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ተጠርተዋል።

በአልጄሪያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሰለሞን አበበ ወደ ናይጄሪያ እንዲሁም አምባሳደር ግሩም አባይ ከሞስኮ ወደ ብራሰልስ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በተመሳሳይ ኃላፊነት ተዛውረዋል።

አምባሳደር አብዱላዚዝ አህመድ ከኩዌት የኢፌዲሪ ኤምባሲ ወደ ሪያድ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ተዛውረዋል።

መንግስት ከሀገሮቹ ጋር ያለው ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ባደረጉት ጉብኝት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መደረሱ ይታወሳል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram