fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የአሜሪካ ጠቅላላ ዕዳ 21 ትሪሊየን ዶላር ደረሰ

የአሜሪካ ጠቅላላ ብሄራዊ ዕዳ 21 ትሪሊየን ዶላር ደረሰ።

ብሄራዊ እዳው እዚህ ቁጥር ላይ ሲደርስ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ከሃገሪቱ ግምጃ ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።፡

ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ዕዳው 19 ነጥብ 9 ትሪሊየን ዶላር እንደነበረ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይም ይህ የብድርና ዕዳ መጠን 21 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል ነው የተባለው።

የፕሬዚዳንት ትራምፕ የ1 ነጥብ 5 ትሪሊየን የግብር ቅነሳና ለሁለት ዓመት የሚቆይ የመንግስት ወጪ ስምምነትን ኮንግረንሱ ማጽደቁ ደግሞ ዕዳው ከዚህም በላይ እንዲጨምር ሊያደርገው ይችላል ተብሏል።

የቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት የባራክ ኦባማ አስተዳደር 11 ትሪሊየን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ እንደተበደረ ግምጃ ቤቱ አንስቷል፡፡

የሃገሪቱ ብሄራዊ ዕዳ በግለሰብ ደረጃ ሲሰላ 64 ሺህ 453 የአሜሪካ ዶላር እንሚደርስም መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

እስከ 2018 መጨረሻ ድረስ ደግሞ ዕዳው 24 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር እንደሚደርስም ግምቱን አስቀምጧል፡፡

ምንጭ፦ አር ቲ እና ከግምጃ ቤቱ ድረ ገጽ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram