የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ቢል ጌትስን በመቅደም የዓለማችን ቁጥር 1 ቢሊየነር ሆነዋል
የኦንላይን የገበያ ስፍራ የሆነው አማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ በ112 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሀብት ቢል ጌትስን በመቅደም የፎርብስ የ2018 ቁጥር አንድ ቢሊየነር ሆኑ።
ባለፉት 24 ዓመታት ለ18 ጊዜያት በፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ቀዳሚ የነበሩት ቢል ጌትስ በ90 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሁለተኛ ሲሆኑ፥ ዋረን ቡፌት በ84 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዳናልድ ትራንፕም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ከነበሩበት 544ኛ ደረጃ በ3 ነጥብ 1 ቢሊየር የአሜሪካ ዶላር ወደ 766ኛ ዝቅ ማለታቸው ነው የተነገረው።
ፎርብስ ባወጣው የቢሊየነሮች ዝርዝር 2 ሺህ 200 ባለሀብቶች 9 ነጥብ 1 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር አስመዝግበዋል ተብሏል።
የሴት ቢሊየነሮች ቁጥርም ከ227 ወደ 256 ከፍ ባለበት በዚህ አመት የዋረን ቡፌት ሴት ልጅ አሊስ ዋልተን በ46 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ቀዳሚዋ ሴት ቢሊየነር መሆኗን ፎርብስ አስታውቋል።
አሜሪካ ብዛት ያላቸው ቢሊየነሮችን ስታስመዘግብ ቻይና ፣ ጀርመን፣ ህንድ እና ሩሲያ በፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ይከተሏታል።
የአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት ብቻ 144 ቢሊየነሮችን ማስመዝገቧም ነው የተነገረው።
ምንጭ፦ cnbc.com
Share your thoughts on this post