የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ጫትን በተመለከተ ያወጣው ጥብቅ ማሳሰቢያ
የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ጫትን በተመለከተ ያወጣው ጥብቅ ማሳሰቢያ-ለሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች
ባህር ዳር፡ መጋቢት 12/2010 ዓ/ም (አብመድ)የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ በማህበረሰቡ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን የጤና እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ጥናቶችንና ትንተናዎችን በማቅረብ የሚከተለውን መልዕከት ልኳል፡፡
የጤና ችግር: የምግብ ፍላጎት መቀነስ-የጫት ተጠቃሚው ላይ ቫይታሚን፣ፕሮቲን ….የመሳሰሉትን ስለማያገኝ ለበሽታ ይጋለጣል፡፡ የመቋቋም ሀይሉ ደካማ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በቀላሉ በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃል፡፤ የሆድ ድርቀት፣ ለአንጀት በሽታዎች ና ኪንታሮት ያጋልጣል፡፤ ለአዕምሮ ህመም መንስኤ መሆንና ማባበስ፣ ከፍተኛ የድካም ስሜት፣ ለተላላፊ በሽታዎች ይዳርጋል፡፡ በቡድን የሚቃም በመሆኑም በትንፋሽ ለሚተላለፉ በሽታዎች እንደ ሳንባ ነቀርሳ ያሉ ይተላለፋሉ፡፡ የስሜት መረበሽና መነጫነጭ፣ ራስን መጣል፣ ለስንፈተ ወሲብ ያጋልጣል፡፡-ስሜት ቢኖርም የመፈጸም አቅሙ የተዳከመ ይሆናል፡፡ ጫት በውስጡ አነቃቂ ንጥረ ነገሮች ሱስ የማስያዝ ባህሪ ስላለቸው ተጠቃሚዎች ደጋግመው እንዲወስዱ ስለሚያደርግ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች በሙሉ እየተባባሱ ይሄዳሉ፡፡
በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት: ከገቢ በላይ ወጭ ማውጣት፣ ቤተሰብን ለችግርና እርዛት መዳረግ፣ በተሰማራበት ስራ ውጤታማ አለመሆን፣ ምርታማነት መቀነስ፣ ለህክምና ከፍተኛ ወጭ ማውጣት፣ ለእህል ማምረቻ የሚውለው መሬት በጫት ስለሚያዝ ለምግብ እህል እጥረት መጋለጥ፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማባዛት ማጭበርበርን መላመድ
በማህበራዊ ኑሮ ላይ የሚያስከትለው ችግር: የቤተሰብ መፍረስ፣ ለጎዳና ተዳዳሪነት መጋለጥ፣ የወንጀል መበራከት
በሌላ ዘርፍ: ሙስናናየስነ-ምግባር ብሉሽነት፣ የመንግስትና የህዝብ ሀብት መመዝበር፣ የወንጀል ድርጊቶች መበራከት
የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በላከው ማሳሰቢያ መሰርት በጫት ምርት የተሰማሩ ዜጎች ተለዋጭ የአኮኖሚ መሰረት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
የህግ ማዕቀፍ ወጥቶለት ክትትልና ቁጥጥር መደረግ አለበት፣ ክልከላ-የሚወጡ ህጎች እንዲከበሩ ማድረግና ከክልሉ የሚመረተውን ጫት በማስቆም ከሌላ አካባቢ የሚገባውን መከልከል፡፡ የማገገሚያ ማዕከላትን መገንባት-በጫት ሱስ ስነ-ልቦናቸው የተቃወሱ ዜጎች ራሳቸውን እንዲያውቅ የሚያስችል የህክምና ማገገሚያ ማዕከል መገንባት በመሆኑም የጤና ጥበቃ ቢሮው ከላይ የተጠቀሱት ምክረ ሃሳቦች ተወስደው እንዲተገበሩ ያልተቆጠበ ጥረት ይደረግ ዘንድ ያሳስባል፡፡
ማሳሰቢያ፡-በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች
የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ
ባህር ዳር