fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የአማራ ክልል ምክር ቤት 43 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2011 የክልሉን መንግስት በጀት አፀደቀ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 43 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2011 የክልሉን መንግስት በጀትን በዛሬው እለት አጽድቋል።

በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የአማራ ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ 3ተኛ ቀኑን ይዟል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎውም የ2011 በጀት ዓመት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ በዛሬው እለት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የ2011 በጀት 43 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል።

በጀቱ 31 ነጥብ 7 በመቶ ከክልሉ፣ 65 በመቶ ከፌዴራል መንግስት፣ 3 በመቶ ደግሞ ከዘላቂ ግቦች ማስመዝገቢያ እንዲሁም 0 ነጥብ 4 በመቶ ደግሞ ከውጭ ሀገራት እርዳታ ይሸፈናል ነው የተባለው።

የዘንድሮው በጀት ከ2010 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ጭማሪ አለው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በእስካሁኑ ቆይታውም የ11 ወራት ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቀርቦ የጸደቀ ማፅደቁም ይታወሳል።

እንዲሁም የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሪፖርት የቀረበለት ምክር ቤቱ ሪፖርቶቹ ላይ ከተወያየ እና ከገመገመ በኋላም አጽድቋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram