fbpx

የኃይሌ ገብረስላሴ የንግድ ተቋም በኮማንድ ፖስቱ ትዕዛዝ ተዘጋ

ዋዜማ ራዲዮ– የታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ኃይሌ ገብረስላሴ ንብረት የሆነ  ሪዞርት በአስቸኳያ ጊዜ አዋጁ ስበብ በኮማንድ ፖስቱ እንዲዘጋ መደረጉን የዋዜማ ሪፖርተሮች አረጋግጠዋል።
በኦሮምያ ክልል ሱሉልታ ከተማ የሚገኘው ያያ ሪዞርት ( Yaya Africa Athletics Village)  ባለፈው ሳምንት የተጠራውን የሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ አገልግሎት በማቋረጡ ሳቢያ የኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጣሪዎች እንዳሸጉትና እስከ ቅዳሜ ምሽት ድረስ ተዘግቶ እንደነበር ተመልክተናል።

ድርጅቱን ለማስከፈት አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረገ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ይህ ጉዳይ በእንጥልጥል ባለበት ወቅት ኃይሌና ሌሎች ለመንግስት ቅርብ የሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች የኢትዮጵያ ቀውስ በሽምግልና እንዲፈታ ሙከራ እያደረጉ የነበረበት ወቅት ነው።
ኃይሌ በመንግስት መገናኛ ብዙሀን ቀርቦ የስራ ማቆም አድማ በሰለጠነው አለም ታይቶ የማይታወቅ የተቃውሞ ስልት ነው ሲል በማጣጣሉ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ እየቀረበበት ስንብቷል።
የተቃውሞው ምክንያት ስራ አጥነት ነው ያለው ኃይሌ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ መክሯል።
ኃይሌ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ትላልቅ የንግድ ተቋማትን ገንብቶ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚሰጣቸው ብስለት የሚጎድላቸው አስተያየቶቹ አትሌቱ ለዓመታት የተጎናፀፈውን ክብር የማይመጥኑ በመሆናቸው ይተቻል።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram