fbpx

የቻይናው ዜድቲኢ በአሜሪካ የተጣለበትን የ1 ቢሊየን ዶላር ቅጣት ሊከፍል ነው

የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ዜድቲኢ በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለበትን የአንድ ቢሊየን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ከሀገሪቱ ጋር መስማማቱ ተገለጸ፡፡

ኩባንያው ላይ ቅጣቱ ሊጣል የቻለው ሀገሪቷ ማዕቀብ ከጣለችባቸው ከኢራንና ሰሜንኮሪያ ጋር የንግድ ልውውጥ አድርጓል በሚል መሆኑ ተነግሯል፡፡

ኩባንያው ወደ ገበያ ከመግባቱ በፊት እንደ ማስያዣ ወይንም መንግስት ያስቀመጣቸው ቅድመሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ እንዲሁም ሁለቱ የገቡት ስምምነት ቢጣስ በሚል 400 ሚሊየን ዶላር ማስያዝ እንዳለበትም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ኩባንያው ከዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንዲያሟሉ ከተቀመጡለት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በ30 ቀናት ውስጥ የቦርድና የስራ አስፈጻሚ ቡድኑን እንዲለውጥ የሚያስገድድ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ ወር ኩባንያው በትራምፕ አስተዳደር ከዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ላይ እስከ 2025 ድረስ እንዳይሳተፍ ታግዶ ቆይቷል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በግንቦት መጀመሪያ ላይ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዢ ጂፒንግ ጋር በመምከር ኩባንያው ዳግም ወደ ገበያ የሚመለስበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ገልጸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

ምንጭ፦ ታይም
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram