የትግራይ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሄዳል

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ጉባኤ ያካሄዳል።

በምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮንፍረንስ አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ታረቀ እንደገለፁት በጉባኤው 2 ረቂቅ አዋጆች ይፀድቃሉ።

በአስቸኳይ ጉባኤው የትግራይ ክልል የስታትስቲክስ ኤጀንሲ እና የጥናትና ምርምር ፖሊሲ ማዕከል በኤጀንሲ ደረጃ ለማቋቋም በወጣው ረቂቅ አዋጆች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ያጸድቃል ትብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ኤጀንሲዎቹን ለማቋቋም ያስፈለገው በመንግስት የሚወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በጥናትና ምርምር ለማስደገፍና የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን በትክክለኛ መረጃ አስደግፎ ለማከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

አስቸኳይ ጉባኤው ነገ ከሰዓት በኋላ በመቐለ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል።

በሙሉጌታ አፅበሃ – ኤፍ.ቢ.ሲ

Share your thoughts on this post

Advertisements
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram