fbpx

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአማራ፤ በኦሮሚያ በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች 500 ሚልየን ብር መደበ

ከ25 ሽህ በላይ ከአማራና ከኦሮሚያ ክልሎች ለተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች ዘላቂነት ያለው መፍትሄ ለማስቀመጥ ኮሚቴዎች ተዋቅረው እየተሰራ መሆኑን የትግራይ ክልል መንግስት ዛሬ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተፈናቃዮች ጉዳይ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃይለ አስፍሃ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ብሄር ተኮር በሆነ ምክንያት ከአማራና ከኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቃሉና ግዚያዊና ቋሚ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ25 ሽህ በላይ የክልሉ ተወላጆች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

ተፈናዮቹን ለማገዝ ግዚያዊ ችግር ፈቺ ፤ ንብረት አሰባሳቢ እንዲሁም ካሣና ዘላቂ መፍትሄ የሚያስቀምጡ ኮሚቴዎች ተቋቁመው እየሰሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ ሃይለ አገላለፅ ሰሞኑን የትግራይ ተፈናቃዮች ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ትክክለኛ ፤ ትዕግስት የተመላበት እና ሊጠይቁት የሚገባቸውን ጥያቄ የጠየቁበት እንደነበር ነው የገለፁት፡፡

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ2011 በጀት ዓመት ለ25 ሽህ ተፈናቃዮች ማቋቋሚያ የሚውል ብር 500ሚልየን መመደቡንም ነው አቶ ሃይለ አክለው የተናገሩት፡፡

በየከተማውና በየገጠሩ ተጠግተው በሚገኙ ተፈናቃዮች በኩል ያለውን የመጠለያና ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የሱቆችና የመጠለያ ማዕከላት በክልሉ መንግስት በመገንባት ላይ መሆናቸውን አቶ ሃይለ አብራርተዋል፡፡

 

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram