fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የትኛውንም ችግር የምንፈታው በመስከን እና ለምን? እና ማን? አደረገው በማለት ነው

የትኛውንም ችግር የምንፈታው በመስከን እና ለምን? እና ማን? አደረገው በማለት ነው፡፡

ግጭቶች ሁሌም አንድ ብሔር ሌላውን ለማጥቃት የሚፈጥሯቸው ችግሮች ብቻ አይደሉም፤ እንዲያ ቢሆን ከሳምንት በፊት ደብረ ማርቆስ የገጠማትን መጠፋፋት ምን ልንለው ነው? የሌላ ሀገር ምስል ለጥፎ ኦሮሞ አማራን አጠፋው የሚልን ተቆርቋሪ የባይሎጂካል መሳሪያ ለቃቂ ያህል እንጠየፈው፤ ***** ስናፍቅሽ አዲስ 

በእርግጥ ባሌ ችግር አለ፤ ግን ችግሩን ከሳምንት በፊት ማርቆስ ከተማ እንደተፈጠረው ችግር እንየው፤ ማርቆስ ሆቴል የቆሙ መኪኖች ሲነዱ እኮ ኮከብ አልባው ባንዲራ የተውለበለበባት አውሮፕላንን በስጦታ የሰጠው ሰው መኪና ተቃጥሏል፤ ለአማራ ተፈናቃዮች ገንዘብ የለገሱ አማሮች ንብረት ወድሟል፡፡

አጥፊዎች በሞኝ አፕታይት ምኞታቸውን ያሳካሉ፡፡ ጠፊዎች ማጥፋት ልክ ይመስላቸዋል፤ ብልሆች የጥፋት አሳብ ከአጥፊው ልብ አውጥተው ሰላም ስለማስፈን ይጨነቃሉ፤ ባሌ ላይ የተነሳው ግጭት ማንም ይጀምረው ማንም ከግጭቱ ብሶ የታየው ግጭቱን ለማስቆምና ግጭቱን ለማስቀጠል የተወሰደው ቅስቀሳ ነው፡፡

ጥፋትን እንደ ነጻነት ትግል አድርገው የቆጠሩ ሰዎች እንዲህ ያለውን ተግባር ሲያወድሱ ሰምተናል፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደምም እንዲህ ያሉ የጥፋት ሀሳቦች ታይተዋል፤ ኦነግ ገባች በሚል ቅስቀሳ ባሌ ፓርክን ለማውደም፣ ሰንቀሌን ለማቃጠል የተደረገው ጥረት ኦሮሞ ስር ተሸሽጎ ከኦሮሞ ሀሳብና የላቀ እሴት ያፈነገጠ እንደሆነ ለመረዳት አይከብድም፤ በሌላ በኩል ስማቸውን እየቀያየሩ እንዲህ ባሉ ግጭቶች ላይ ቤኒዚል የሚያርከፈክፉ ብዙ ናቸው፡፡

በአንድ ስም አንዴ ጠቡ የነጻነት ተጋድሎ መሆኑን ጽፈው በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮሞ አማራን አጠፋ በሚል መረጃ የሚለቁ የሌባ ዓይነ ደረቆችንም አይተናል፡፡

እንደ አብረሃ ደስታ ያሉ ደግሞ የቄሮ ጥያቄ ስላልተመለሰ ነው እያሉ እያወደሱት ነው፡፡ አንዳንዶች የውጪ ምስሎችን የበርማ ሙስሊሞችን ጥቃት የሚያሳዮ ፎቶ ግራፎችን ጭምር በመልቀቅ ባሌ ጎባ አማራ ላይ የተፈጸመ እልቂት እንደሆነ የለቀቁት መረጃ ብዙ ሰካራም የፌስ ቡክ አክቲቪስቶች ትክክል መረጃ ነው ብለው ሳይቀደሙ ለመቅደም እያራገቡት ነው፡፡

የሆነውን ለማስቆም ያልሆነ ሆነ በማለት የሚመጣ ሰላም የለም፤ ጥፋቱን ለማባስ ሆ ከሚል ሰው ጀርባ ብዙ ምስጢር ይኖራል፤ ባሌ ላይ ስንጋጭ አዋሽ እና ጅግጅጋ እኮ ኮንትሮባንድ ዶላር እየተያዘ ነበር፡፡

አሁንም አርቀን ማሰብ ይኖርብናል፤ ከማናውቀው ተቆርቋሪ ነኝ ባይ ችግር የማባባስ ዜና የምናውቀው ወገን ይበልጥብናል፡፡ አንድ ህዝብ ነን፡፡ ትግሬ አማራ ኦሮሞ እየተባባልን መጠፋፋት የለብንም፤ የብልጥ አሻንጉሊት ማለት የሚሰራውን የማያውቅ ሞኝ ነው፡፡ ራስን ከማጥፋት፣ ስለመጠፋፋት ከመስበክ በላይ ሞኝነት የለም፡፡ DireTube

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram