የትራምፕ የኢኮኖሚ አማካሪ ስልጣን ለቀቁ – Key Trump Economic Policy Adviser Resigns
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ የኢኮኖሚ አማካሪ ግሬይ ኮህን ስልጣን መልቀቃቸውን ዋይት ሐውስ አስታወቀ።
የኮህን ስልጣንን መልቀቅ በቅርቡ ትራምፕ ከውጭ በሚገቡ የብረትና አልሙኒየም ምርቶች ላይ ለመጣል ካቀዱት ቀረጥ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ግምቶች እየወጡ ነው።
የ57 ዓመቱ ኮህን ባለፈው ዓመት ትራምፕ ላደረጉት የግብር ማሻሻያ ከፍተኛ አስተዋጥዖ ካበረከቱት መካከል አንደኛው መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ኮህን በሰጡት መግለጫ አገራቸውን በማገልገልቸው ትልቅ ክብር እንደሚሰማቸው ገልጸው የአሜሪካ ህዝብ በግብር ማሻሻያው እንደሚጠቀምም ተናግረዋል።
የቀድሞ የጎልድ ማን ሳክ ፕሬዚዳንት ኮህን “ፕሬዚዳንት ትራም ምርጫቸው ስላደረጉኝ አመሰግናለው፤ ወደፊት መልካም እድል እንዲገጥማቸው እመኛለው” ብለዋል።
ኮህን በቅርቡ ስልጣን የለቀቁ ሌላኛው ከፍትኛ የስራ ኃላፊ ሆነዋል።
US President Donald Trump’s top economic adviser Gary Cohn is resigning, the White House has said.
It is the latest in a series of high-profile departures from President Trump’s team.
There has been speculation that Mr Cohn, a supporter of free trade, was angered by Mr Trump’s plans to impose tariffs on aluminium and steel imports.
In a statement released by the White House, Mr Cohn said it had been “an honour to serve my country”.
The 57-year-old former president of the Goldman Sachs bank had helped Mr Trump push through his sweeping tax reforms late last year.
ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ