የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
በዛሬው እለትም ከኢፌዴሪ አቻቸው ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ።
የሁለቱ አገራት ሁለተኛው የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም በዛሬው እለት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄድ ይሆናል።
የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በቴክኒካል ኮሚቴ ደረጃ ላለፉት ሁለት ቀናት ምክክር አድርገዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል የፖለቲካ ምክክር ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኤፍ.ቢ.ሲ
Share your thoughts on this post