fbpx
AMHARIC

የተሻሻለው ብላክቤሪ ስልክ ዋና ስራ አስፈጻሚው ላይ የእድሜ ልክ እስራትን ጋርጦበታል

የተሻሻለው ብላክቤሪ ስልክ ዋና ስራ አስፈጻሚው ላይ የእድሜ ልክ እስራትን ጋርጦበታል

በኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ የተፈበረከው እጅግ ደህንነቱ የተጠበቀ የስማርት ስልክ ፋንተም ሴኪዩር (Phantom Secure) በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ አደገኛ በሚባሉ ግለሰቦች እጅ ለህገ-ወጥ ተግበራ በመዋሉ ተከትሎ ክስ ቀርቦበታል፡
የአሜሪካ ባለስልጣናት አውቆ ለወንጀል ተግባር ታስቦ የምስጠራ ቴክኖሎጂ የተሰራ ነው በሚል ተቋም ላይ ያነጣጠረ ክስ ለመጀመሪያ ጊዜ አቅርበዋል፡፡

የአሜሪካው የፍትህ ቢሮ የተሸሻለውን የብላክቤሪ ፋንተም ሴኪዩር ምርት የፈጠረውን ቪንሰንት ራሞስ እና 4 ተባባሪዎቹን ባለፈው ሳምንት በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ ግለሰቦቹም የፋናተም ሴኪዩር ስልክ ለአደንዛዥ እጽ ማዘዋወሪያ እንዲውል ሆን ብለው ምርቱን በመስራት እና በሴራ ተሳታፊ መሆን በሚሉ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ፋንተም ሴክዩር ስልክ ዲዛይን የተደረገው ሆን ተብሎ አለም አቀፍ የአደንዛዥ እጽ ዝውውርን ለማፋጠን ተብሎ በተቋሙ ሆን ተብሎ የተሰራ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም 20,000 የፋንተም ሴክዩር ምርት በአለም አቀፍ ደረጃ መሰራጨቱ ተነግሯል፡፡
በግለሰቦቹ ተፈጽመዋል የተባሉበት ሁለቱም ክሶች እስከ የእድሜ ልክ እስራት ዘብጥያ የሚያቆይ ወንጀል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
መቀመጫውን በካናዳ ያደረገው ተቋሙ ከፋንተም ሴኪዩር (Phantom Secure) በአስር ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ያከናወነ ሲሆን የተሻሻለውን የብላክ ቤሪ ምርቱ እጃቸው ከገባ አደገኛ ቡድኖች መካከልም ሲናሎዋ ካርቴል (Sinaloa Cartel) የተባለው አለም አቀፍ እጽ አዘዋዋሪ እንዱ መሆኑን የወንጀል መርማሪዎች ገልጸዋል፡፡

ፋንተም ሴኪዩር የስልኮችን መሰረታዊ ተግባራት የሆኑ እንደ የድምጽ አገልግሎቶች ፣ ማይክራፎን፣ ጂፒኤስ ፣ ካሜራ፣ ኢንተርኔት እና መተግበሪያዎች ስልኩ አጭር የጽሁፍ መልእክት አገልግሎቶች በሚሰጥበት ወቅት የሚያቋርጥ መሆኑ ታውቋል፡፡

 


ምንጭ: -ቢቢሲ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram