fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የብሪታንያው መከላከያ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

የብሪታንያው መከላከያ ሚኒስትር ጋቪን ዊሊያምሰን በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

ሚኒስትሩ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ሞቱማ መቃሳ ጋር በሁለቱ ሃገራት መካከል ስላለው ጠንካራ ወዳጅነት ተወያይተዋል።

ሃገራቸው በሶማሊያ ለአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) እያደረገች ባለው ድጋፍ እየተሰራ ያለውን ስራም ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ሃገራቸው በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

ሴቶች በሰላምና ደህንነት የላቀ ሚና እንዲጫወቱም ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ኢትዮጵያ ብሎም የቀጠናው ሃገራት እያደረጉት ያለውን ጥረት ታግዛለችም ብለዋል።

የተጠናከረችና ደህንነቷ የተጠበቀ አህጉርን ለማየት በሚደረገው ጥረትም ሃገራቸው እያደረገች ባለው ድጋፍ የተገኘውን ውጤትም አድንቀዋል።

ብሪታንያ ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚኖራት መልካም ግንኙነትም ሰላም የሰፈነባት ቀጠና ብሎም አለም ለማየት ያግዛልም ነው ያሉት።

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram