fbpx

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅ ተቋም ተማሪዎች ንብረት ከማውደም እንዲቆጠቡ ዩኒቨርሲቲው አሳሰበ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ በማቅረብ በዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀረበ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አራጋው ብዙዓለም እንዳሉት፥ ተማሪዎቹ አሁን ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሆነዋል።

ጉዳዩን በግቢ ፖሊሶች መቆጣጠር አልተቻለም ያሉት አቶ አራጋው፥ ሁኔታውን ለማረጋጋት የአድማ በታኝ ፖሊስ ወደ ግቢው መግባቱን ተናግረዋል።

አሁን ላይም ተማሪዎች በየመኖሪያ ክፍሎቻቸው እንዲገቡ ማድረግ መቻሉንም ነው የተናገሩት።

ሃላፊው አያይዘውም ተማሪዎቹ ንብረት ከማውደም እንዲቆጠቡና ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እያስመከርን ነው ብለዋል።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም ተማሪዎች ከሌላው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለየ አግባብነት የሌለው ፈተና እየተፈተንን ነው በማለት ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram