fbpx

የባህረ ሰላጤው ሀገራት የኢኮኖሚ ቀውስ ለጋጠማት ዮርዳኖስ 2 ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላር ሊለግሱ ነው

ሦስት የባህረ ሰላጤው ሀገራት ኩዌይት፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለዮርዳኖስ በእርዳታ መልኩ 2 ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላር ሊለግሱ ነው፡፡

ዮርዳኖስ ከዚህ ቀደም የመንግስት ወጪ ቅነሳ ዕቅድ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ህዝብ ሲቃወመው ሰንብቷል፡፡

እንዲሁም ተቃውሞውን ተከትሎ የዮርዳኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃኒ አልሙሊኪ ከስልጣን መውረዳቸውም ይታወሳል፡፡

ታዲያ የሀገሪቱ ሁኔታ ያሳሰባቸው የባህረ ሰላጤው ሀገራት በመካ ተገናኝተው ከተወያዩ በኃላ ነው እርዳታው ይፋ የሆነው ተብሏል፡፡

ገንዘቡም በጥሬ መልኩ በቀጥታ በዮርዳኖስ ማዕከላዊ ባንክ ውስጥ ይቀመጣል ተብሏል፡፡

የአሁኑ የገንዘብ ድጋፍ የተጎዳውን የዮርዳኖስ ዓመታዊ የበጀት ጉድለት እንዲያገግም ያደርገዋል ተብሏል፡፡

የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዳላህ ሁለተኛ ሃኒ አልሙሊክን ካሰናበቱ በኃላ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩትን ኦማር አል ራዛዝን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾሙ ሲሆን፥ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም አዲስ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማድረግ ውይይት መያዛቸው ተነግሯል፡፡

 

 

ምንጭ፥አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram