የቃር ህመምና መከላከያ መንገዱ

በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜትን በማስከተል የሚከሰተው የቃር ህመም በአብዛኛው የተለመደና ተደጋጋሚ ችግር ነው።

ይህ ህመም አብዛኛውን ጊዜ ምግብ ከተመገቡ በኋላ በተደጋጋሚ ይከሰታል።

ከዚህ ባለፈም በመኝታ ሰዓት በድንገት ሊከሰት የሚችል የህመም ስሜት ነው።

ህመሙ አብዛኛውን ጊዜ በጨጓራ ውስጥ ያለው አሲድ ወደ ላይኛው ምግብ አስተላላፊ ቱቦ ሲገባ እንደሚከሰት የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይህ ህመም የተለመደ ቢሆንም የህክምና ባለሙያዎች ግን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምክንያት መሆናቸውን ይገልጻሉ፤

ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ፣ ሽንኩርት ማብዛት (በተለይም በጥሬው ሲመገቡት ለዚህ ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ።

ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ማብዛት፣ የአልኮል መጠጦችን በተደጋጋሚ መውሰድ፣ የማነቃቃት ባህሪ ያላቸውን መጠጦች ማብዛት እንዲሁም ከልክ በላይ አብዝቶ መመገብ ለዚህ ህመም ይዳርጋል።

በተጨማሪም ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት የተጋለጡ ሰዎች እና ሴቶች በእርግዝና ወቅት ለዚህ ህመም ይዳረጋሉ።

በዚህ ህመም ሲዳረጉ ምናልባትም ለመዋጥ መቸገር፣ ደረት አካባቢ ማቃጠል፣ ሆድ አካባቢ ምቾት ማጣት፣ የጉሮሮ አካባቢ የመጎምዘዝ እንዲሁም በፈሳሽ መልክ የተመገቡት አፍ እና ጉሮሮ ላይ የተከማቸ የሚመስል ስሜት ይከሰታል።

አልፎ አልፎም የትንፋሽ መቆራረጥ የማላብና የድካም ስሜት ሊከሰትም ይችላል።

ቃርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ይህን ህመም አመጋገብን በማስተካከል እና ስሜቱን የሚያመጡ ወይም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ መከላከል ይቻላል።

በዚህ መልኩ የተከላከሉት ህመም የተለየ ስሜት ማለትም በበዛ ሁኔታ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣ ያዝ የማድረግ ስሜት፣ ትከሻ አካባቢ የህመም ስሜት እንዲሁም የትንፋሽ መቆራረጥ የሚያስከትል ከሆነ ሃኪም ያማክሩ።

ከዚህ ባለፈም የቃር ስሜቱ ተደጋጋሚ ከሆነ፣ በዚህ ሳቢያ የማቅለሽለሽና የማስመለስ ስሜት ካለ፣ ለመመገብ ከተቸገሩ እና ተደጋጋሚ ጊዜ መዋጥ የሚያስቸግርዎ ከሆነ ሃኪም ማማከርን አይዘንጉ።

አመጋገብን ማስተካከልና ህመሙን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን አለማድረግና በመኝታ ሰዓት ደግሞ ቀደም ብሎ መመገብና ሲተኙም ትራስዎን ከፍ ማድረግን አይዘንጉ።

 

 

 

ምንጭ፦ medicinenet.com

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram