fbpx

HT

ሐበሻ ታይምስ ሚዲያ

AMHARIC

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ለምርጫ ቅስቀሳ በህገወጥ መንገድ ከቀድሞ የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙአመር ጋዳፊ በሚሊዮን ዩሮዎች የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ለጥያቄ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። እ.ኤ.አ በ2007 በፈረንሳይ በተደረገው የምርጫ ቅስቀሳ ሳርኮዚ ምርጫውን ለማሸነፍ ባደረጉት የምረጡኝ ትቅስቀሳ ከሊቢያና ከሌሎች በሕገ ወጥ መንገድ ሚሊዮን ዩሮዎችን ተቀብለዋል በሚል ዛሬ ለጥያቄ ፖሊስ ጣቢያ መሄዳቸው ተገልጿል።

በቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ላይ ምርመራ የተጀመረው ፈረንሳይ ባለፉት አስርት አመታት በፖለቲካ ማጭበርበር ከፍተኛ ፋይናንስ አድርጋለች መባሉን ተከትሎ ነው። ኒኮላስ ሳርኮዚ ግን ክሱን ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። የ63 አመቱ ሳርኮዚ እ.ኤ.አ በ2007 ላካሄዱት የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ የቀድሞ የሊቢያ ፕሬዝዳንት ሞአመር ጋዳፊ በድብቅ 50 ሚሊዮን ዩሮ ሰጥተዋቸዋል የሚል ምርመራ ቀርቦባቸዋል።

ገንዘቡ ለምርጫው በሕጋዊ መንገድ ከተመደበው ከእጥፍ በላይ መሆኑ ተመልክቷል። በክፍያው የፈረንሳይ የውጭ የፋይናንስ ሕግ በመጣስ ሊጠየቁ ይችላሉ ተብሏል። የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ከአውሮፓውያኑ 2007 እስከ 2012 ፈረንሳይን በፕሬዝዳንትነት መምራታቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ፤ ዘ ጋርዲያን

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram