fbpx
AMHARIC

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ለፕሬዚዳንትነት መወዳደር ይፈልጋል

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊ በሊቢያ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ይፈልጋል።

ሙአመር ጋዳፊ በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ፊታውራሪነት በተካሄደ የእርስ በርስ ግጭት ከስልጣን ተወግደው ህይወታቸውንም ካጡ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል።

በዚህም ሊቢያ የቀድሞ መሪዋን ሙአመር ጋዳፊን ከስልጣን ካስወገደች በኋላ የራቃትን ሰላም ዛሬም አላገኘችም።

በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲ ሲ) በሰብአዊ መብት ወንጀል የሚፈለገው ሰይፍ ጋዳፊ፥ ሀገሪቱን ከገባችበት ቀውስ ለማውጣት በሊቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ሊሳተፍ እንደሚችል ነው የተገለፀው።

የጋዳፊ ሁለተኛ ልጅ የሆነው የ45 አመቱ ሰይፍ አል ኢስላም አሁን ላይ በቱኒዝያ ውስጥ በስደት እየኖረ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በስደት ከሚኖርበት ሀገር በመሆን በቀጣዩ የሊቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊሳተፍ እንደሚችል መናገሩ ተሰምቷል።

ሰይፍ ጋዳፊ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በሀገሪቱ የሊቢያ ህዝቦች ነፃ አውጪ (ፒ ኤፍ ኤል ኤል) በመባል በሚታወቀው ፓርቲ ታቅፎ ይወዳደራል ነው ተብሏል።

በዚህም ሊቢያን ለመታደግ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው የሚሳተፍ መሆኑ እና ሀገሪቱ ወደ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት ያለውን እቅድ ለሊቢያ ህዝብ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ rt.com

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram