fbpx

የስፔን ፖሊሶች ሜዲትራኒያ ባህር ላይ ከ500 በላይ ሰዎችን መታደጋቸውን አስታወቁ

ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበሩ ከ500 በላይ ሰዎችን ሜዲትራኒያ ባህር ላይ መታደጋቸውን የስፔን ፖሊሶች አስታወቀ፡፡

የስፔን ባህር ኃይል ከስምንት ትንንሽ ጀልባዎች ላይ 243 ሰዎችን መታደጋቸውን ገልጸው፥ ከአንድ ቀን በኃላ በድጋሚ ከዘጠኝ የተለያዩ ጀልባዎች 293 ሰዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በነፍስ አድን ስራው ላይ አውሮፕላንና ሄሊኮፕተር መሰማራታቸውን የስፔን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቹ ከተለያዩ ሀገራት የሄዱ ሲሆን፥ አብዛኞቹ ከሰሜን አፍሪካና ከሰሃራ ሀገራት በታች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከ2018 ጀምሮ ወደ ስፔን ለመግባት የሞከሩ 6ሺህ 872 ስደተኞችን የነፍስ አድን ጥረት የተደረገ ሲሆን፥ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም የ218 ሰዎች ህይወት ማለፉንም በመረጃው አስፍሯል፡፡

ስፔን ኢጣሊያንና ግሪክን በመከተል ወደ አውሮፓ ለማቅናት በሚደረጉ የባህር ላይ ጉዞዎች የስደተኞች ሦስተኛዋ መዳረሻ ሀገር መሆኗን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

ምንጭ፦አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram