fbpx

የስፔን ላሊጋ ሻምፒዮኑ ባርሴሎና በኔልሰን ማንዴላ 100ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ የዋንጫ ጨዋታ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ገብቷል

የካታላኑ ባርሴሎና ኮከቦቹን ሊዮኔል ሜሲን እና ሉዊስ ሱዋሬዝን ጨምሮ በኦሊቨር ሬጊናልድ ታምቦ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ተጫዋቾችም በርካታ ህዝብ አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን በፀጥታ አስከባሪዎችና በፖሊሶች ጥበቃ ታጅበው ወደ ማረፊያቸው ሄደዋል።

ባርሴሎና በደቡብ አፍሪካ በሚኖረው ቆይታ ስፔን የ2010 የዓለም ዋንጫን ባነሳችበትና ሶከር ሲቲ በመባል በሚጠራው ግዙፉ ኤፍ ኤን ቢ ስታዲየም ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ይጫወታል። ክለቡ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ግጥሚያ ሲያደርግ የአሁኑ ሁለተኛው ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 2007 ከሰንዳውንስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።

የፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴውን በመምራታቸው ምክንያት በሮቢን ደሴት ለ27 ዓመት በእስር ያሳለፉት ኔልሰን ማንዴላ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር 2013 በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ቢቢሲ ስፖርት

Share your thoughts on this post
%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram