የሴራሊዮን ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መካሄድ ተጀምሯል

በመጀመሪያ ዙር የሴራሊዮን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ እጩዎች አሸናፊ ሊያደርጋቸው የሚችለውን በቂ ድምጽ ማግኘት ባለመቻላቸው ዛሬ ሁለተኛው ዙር ምርጫ ተጀምሯል፡፡

አሁን ስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኤርነስት ቢያ ኮሮማ ሃገሪቱን ለ10 ዓመታት ከመሩ በኋላ ስልጣን እንደሚለቁ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው ሳሙራ ካማራ እሳቸውን ተክተው እንዲወዳደሩ በፓርቲያቸው የተመረጡት፡፡

የሳሙራ ካማራ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ደግሞ ጂሊዬስ ማዳ ቢዮ ናቸው፡፡

በመለመሪያ ዙር ምርጫ ጂሊዬስ ማዳ ቢዮ 43.3 ከመቶ ድምጽ አግኝተው ነበር፡፡

ጂሊዬስ ማዳ ቢዮ በፈረንጆቹ 1994 እና 1996 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣ ይዘው ነበር፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Share your thoughts on this post

%d bloggers like this:
Visit Us On TwitterVisit Us On YoutubeVisit Us On Instagram